የኢትዮጵያ መንግስት ይመካባቸው ከነበሩ የልማት ዕቅዶች መካከል በግል ባለሀብቶች የሚለማ የእርሻ ኢንቨስትመንት አንዱ ነው። ይህ አወዛጋቢ የልማት እቅድ ከፍተኛ ደንቃራ ገጥሞታል። ሶስት መቶ ሺ ሄክታር መሬት ወስጄ አለማለሁ ብሎ የነበረው ካራቱሪ(KARATURI) የተባለ የህንድ ኩባንያ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብቷል። ሀብት ንብረቴን ይዤ ከኢትዮጵያ እንድወጣ ይፈቀድልኝ ሲል ለጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ደብዳቤ ፅፏል። የህንድ ፕሬዝዳንት በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከሚነጋገሩባቸው ጉዳዮች አንዱ የካራቱሪ ኩባንያ ጉዳይ መሆኑንም ስምተናል።ዝርዝር አለን

LEAVE A REPLY